ሁሉም
ለኣንድነት
ከምድራዊነታችን ባሻገር
Beyond Our Earthly Realm
ጸረ ምድራዊ ስበት
ጸረ ምድራዊ ስበት
ልቦናችሁን ከፍ ከፍ አድርጉ
ልቦናችሁን ከፍ ከፍ አድርጉ
All
for Unity
እምነታችን-
"እውነት
ነጻነት
እኩልነት
ሕብረት
ጽድቅ
ሰላም
ፍቅር"
Our Belief-
"Truth
Freedom
Equality
Solidarity
RighteousnessPeace
Love"
"..እንደኛ አንድ
ይሆኑ ዘንድ
በስምህ
ጠብቃቸው።"
ዮሐ. 17፥11
"....protect them by the power of your name - the name you gave me - so that they may be one as we are one." John 17: 11
ከዚህ ይጫኑ
ሄኖክ ኢትዮጵያዊ - ኤርትራዊ
እውቀት እና ሥልጣኔ፥ ማንነት እና ድኅነት
መግቢያ
ስለ ምድራዊ እውቀት አመጣጥና አካሄድ ስናስተውል፥
ባንድ በኩል ምድራዊ ሕይወታችንን ሲያሻሽል፥
በሌላም በኩል መንፈሳዊ ሕይወታችንን ሲያጣጥል፥
ሙሉ ሆኖ የተፈጠረን ሰው እንዲህ ከሁለት ሲከፍል፥
ምድራዊ እውቀት እና የዘመኑ ሥልጣኔም ትርጉም ያጣል።
የሰው ኑሮ ከራሱ በመነጨ እውቀቱ እንዳይሆን፥
በራሱ ካገኘው እውቀት ውስጥ ጣልቃ የገባውን፥
ተፈጥሮአዊ ማንነቱን የወሰደበትን - ወይንም አደናብሮ የቀየረበትን፥
እስቲ እንመልከተው፥ የሰውን ምድራዊ እውቀቱን፥
ከጥንት ከአመጣጡ ጀምረን፤
ከጻዲቁ ሄኖክ መልእክትና አቤቱታ ተነስተን።[1]
እንዲሁም እንመርምር ታሪካዊ ሂደቱን፤
እውቀታችን በኛነታችን ላይ ያስከተለውን - ተፅንኦውን።
በመጨረሻም፥ ኃይልና ሥልጣን፥ የእግዚአብሔር መሆኑን አውቀን፥
ድኅነት የሚገኝ ከእርሱ መሆኑን አምነን፥
ፍቅር፥ ሰላም፥ ጤንነትና ደስታን እንማጸናለን።
[1] “አቤቱ ረድኤቴ መድኃኒቴም፥ የአፌ ቃልና የልቤ ሃሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን።” መዝ. 18 (19)፡ 14
ሁሉንም ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ